የአካል ጉዳተኞችን እና ተጋላጭ ሴቶችን ሕይወት በዘላቂነት ለማሻሻል ያለመ የሁለት ዓመት የሁለትዮሽ ስምምነት ተደረገ፡፡

Announcments

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ሰክሰስ ፕላስ ሀገር በቀል የተራድኦ ድርጅት መካከል የአካል ጉዳተኞችን እና ተጋላጭ ሴቶችን ሕይወት በዘላቂነት ለማሻሻል ያለመ የሁለት ዓመት ስትራቴጂካዊ የትብብር ስምምነት ተፈራርመዋል ።

በስምምነቱ ወቅት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የማህበራዊ ዘርፍ ሚኒስቴር ድኤታ ክብርት ሁሪያ አሊ እንደገለፁት በአካል ጉዳተኞች ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ መንግስት ከሚተገብራቸው ስራዎች በተጨማሪ ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

መሰል ስምምነቶች የአካል ጉዳተኞችን ችግር ከማቃለል ባሻገር ዜጎችን ዘላቂ አስተማማኝ በሆነና በተቀናጀ መልኩ በመደገፍ ሀገሪቱ ያላትን የሰው ሀይል በመጠቀም ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ ረገድ የጎላ ሚና እንደሚኖረው ገልፀዋል።

በስምምነቱ ከተካተቱ ዋና ዋና ነጥቦች መካከል ሰክሰስ ፕላስ ሀገር በቀል የተራድኦ ድርጅት የአካል ድጋፍ መሳሪያዎችን በተመረጡ ክልሎች ለሚገኙ አካል ጉዳተኞች ዊልቸሮች ለተጠቃሚዎች ማድረስ፣ የኢኮኖሚ አቅምን ለመገንባት የገበያ ፍላጎትን ያገናዘበ የሙያ እና የሥራ ፈጠራ ሥልጠና የሚሰጥ የኢኮኖሚ ማጎልበቻ፣ ፕሮግራም ይተገበራል፡፡

በተጨማሪም የአካል ጉዳተኞችን መብት ለማስከበር እና ግንዛቤን ለማሳደግ ለሁለት ተከታታይ ዓመታት ዓለም አቀፍ የአካል ጉዳተኞች ቀን በጋራ ማክበርን ያጠቃልላል፡፡


IMG_0847
previous arrow
next arrow