ሰክሰስ ፕላስ ቻሪተብል ኦርጋይዜሽን የትንሳኤ መታሰቢያ በዓልን ምክንያት በማድረግ በትንሳኤው ዋዜማ ጉዳት ደርሶባቸው በህክምና ላይ ለሚገኙ የፌደራል ፓሊስ አባላት ስጦታ አበረከተ።
የትንሳኤ በዓል ስጦታው ሲበረከት የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ጠቅላይ አዛዥ ክቡር ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል፤ ስትራቴጂክ አመራሮች እና የፌደራል ፖሊስ የማኔጅመንት አባላት የተገኙ ሲሆን የሰክሰስ ፕላስ ቻሪተብል ኦርጋናይዜሽን መስራች እና ዳይሬክተር አቶ ፍሬው መንገሻ በስፍራው በመገኘት ሀምሳ ዊልቸሮችን አበርክተዋል።
በመጨረሻም ሰላምን ለማስጠበቅ ቀን ከለሊት እየተጉ ጉዳት ለደረሰባቸው የሕዝብ አገልጋዮች በጎ እንድናደርግ እድል ስለሰጣችሁን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ጠቅላይ አዛዥ ክቡር ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል እና የፌደራል ፖሊስ የማኔጅመንት አባላትን በሰክሰስ ፕላስ ቻሪተብል ኦርጋናይዜሽን ስም ከልብ እናመሰግናለን።





