ሰክሰስ ፕላስ ቻሪተብል ኦርጋናይዜሽን ወደ ምስራቋ ፈርጥ ሀረር ከተማ በማቅናት ለአካል ጉዳተኞች በርካታ የሚልቸር ድጋፍ አደረገ።

Uncategorized

ሰክሰስ ፕላስ ቻሪተብል ኦርጋናይዜሽን ከሴቶች እና ማሕበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት በቀረበለት ጥሪ መሰረት በርካታ ዊልቸሮችን በሀረሪ ክልል ለሀረር ከተማ አካል ጉዳተኛ ወገኖቻችን ያበረከተ ሲሆን፤

በዕለቱ የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ድኤታ ወ/ሮ ሁሪያ አሊ፤ የጤና ሚኒስትር ሚኒቴር ድኤታ ክቡር ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ፤ የክልሉ ፕሬዝዳንት የተከበሩ አቶ ኦርዲን በድሪ፤ ካቢኔዎቻቸው እና ሌሎችም የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊዎች በተገኙበት የእውቅና ሰርተፍኬት ተበርክቶለታል።

የዕውቅና ሰርተፊኬቱንም የሰክሰስ ፕላስ ቻሪተብል ኦርጋናይዜሽን መስራች እና ዳይሬክተር አቶ ፍሬው መንገሻ ከክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ ኦርዲን በድሪ እና ከጤና ጥበቃ ሚኒስትር ሚኒስቴር ድኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ እጅ ተቀብለዋል።

በመጨረሻም ስመ ጥሩ የአብረ በሃታ ማገገሚያ ማዕከል በዕለቱ ዳግም ስራ በመጀመሩ የተሰማንን ደስታ ልንገልፅ እንወዳለን።